Snack's 1967
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

ጥሩ ጓደኛ ለመምረጥ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

✍ በወጣቱ ተልዕኮ(አህመድ የሱፍ)
Iqra

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ጓደኛህ ማን እንደሆነ ከነገርከኝ ማንነትህን እነግርሃለሁ!!!

እኛ የሰው ልጆች ማህበራዊ ፍጡሮች እንደመሆናችን ጓደኞች እንዲኖሩን እንፈልጋለን። አብዛሃኛዎቻኛው የሂወታችን ክፍል ከሰዎች ጋር በመቀላቀል ወይም ማህበራዊ ትስስር ከመፍጠር ጋር የተያያዘ ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ እንደሚታወቀው ማህበራዊ ኑሮ በራሱ የጤናማ አኗኗር እና የችግር መፍትሄ ዋነኛ መሳሪያ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሂወት ውጣ ውረድ የበዛበት የችግር ፣ የተስፋቢስነትና የውድቀት መንስኤም ነው።

ታዲያ ይህ ማህበረሰብ አባት ፣ እናት ፣ ልጅ ፣ እህት ፣ ወንድም ፣ አክስት ፣ አጐት ፣ ጓደኛ ፣ ጐረቤት እያለ የሚፈጠር ማህበራዊ ትስስር ሲሆን ይህ ትስስር ከጊዜ አንፃር እና እንደ የሰው ባህሪ እየተወሳሰበ ሂወት በፈተና የተሞላች ሆና መጥፎ ነገሮችን እንድንጋፈጥ እንሆናለን።

በጥሩም ይሁን በመጥፎ በጓደኞቻችን ተፅእኖ ሥር እንወድቃለን። ይህ ደግሞ ልናስተባብለዉ የማንችል ሀቅ ነዉ። ከመጥፎ ተፅእኖ ራሳችነን ነፃ ለማድረግ ጓደኛ የምንመርጥበትን መስፈርት ልናስተካክል ይገባል።

ከጓደኞቻችን ጋር ወደ ተሻለና መልካም ወደ ሆነ ነገር ለመድረስ ዛሬ ላይ ምን አይነት ጓደኛ መምረጥ እንዳለብን መወሰን ይኖርብናል። አለበለዚያ ግን በጓደኞቻችን እና በእኛ መካከል ያለው ጉዞ የቅፍለቶች ጉዞ ነው የሚሆነው።

ለዚህም ነበር የአሏህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ለምንመርጣቸዉ ጓደኞቻችን ትኩረት እንድንሰጥ የመከሩን። ጓደኞቻችን በሙሉ የአሏህን መንገድ እንዳንዘነጋ የሚያስታዉሱን መሆን ይኖርባቸዋል።

የአሏህ መልእክተኛ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) መርጠዋቸዉ የነበሩት ሰሃቦች በጠቅላላ ከርሳቸዉ ጋር እስከ መጨረሻዉ የዘለቁትን እና በተልዕኴቸዉም ተስፋ ያልቆረጡትን ነበር።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከገለፁዋቸዉ ዓርሽ ጥላ ስር ከሚቀመጡት ሰባት አይነት ሰዎች አንዱ ለአሏህ ብለዉ የተዋደዱ ሁለት ጓደኛሞች ናቸዉ።

ለዚህ ዉዴታዉ መሠረቱ የነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ንግግርን ነዉ።

ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) በቡኻሪ ጥራዝ 1, መጽሐፍ 2, የሐ.ቁጥር 12 ላይበተዘገበው ሐዲስ "ከናንተ አንዳችሁ ለራሱ የሚወደዉን ነገር ለወንድሙ እስካል ወደደ ድረስ አላመነም" ብለዋል።

ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በጉዞ አጋሮቻቸዉ ጓደኛ ለመምረጥ ምንድ ነዉ መሥፈርቱ? ተብለዉ ተጠይቀዉ ተወዳጁ የአሏህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) "ያን ጓደኛ ምረጥ: ባየኽዉ ወቅት አሏህን የምታስታዉስበት፤ ከእሱ ጋር ባወራህ ወቅት ስለ አሏህ ያለህን እዉቀት የሚጨምርልህ እና ከሞት ቡኋላ ላለዉ ተጠያቂነት አስታዋሽህ የሆነዉን" ብለዋል።

2031

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ